Official Ticket Sale is Open
Bayalew EP Release Party 28 Oct 2023

(powered by Chapa)

ሠላም ነን፥ ሰላም ናችሁ? እኛ ነገስታት እንባላለን። በልጅነት አንደበታችን “ነገስታት” ብለን የጀመርነዉ ‘ሀ’ መንገዳችን ፥ ጊዜ ጊዜን እየወለደ ዛሬ ላይ አድርሶናል ።የፈጣሪ ፍቃድ ሆኖ እንደ ልጅ እግር ሳይሆን ምራቁን እንደ ዋጠ አዛዉንት ሰዉ ሞገሱን አላብሶ ካባዉን ደርቦ ያለ እድሜያችን ክብር ለሰጠን “አንድዬ” ምስጋና እየሰጠን ፥ የጥንቱን የአበዉን ባህል እና ትውፊት በአደራ መልክ ከመዛግብት ድርሳናት እና ከአባቶች ተረክበን፣ ላለንበት ዘመን በልኩ ሸምነን ፣ እየሰፋን ለማልበስ ደፋ ቀና ማለት ከጀመርን ሰነባብተናል። ቃል ትልቅ የህሊና እዳ ነዉ እና በቃል ያገኘናትን ኢመንት ትንሽ ጥበብ ዘመናች በፈቀደልን የድምፅ እና የምስል ማሰራጫን እንደ ድልድይ ተጠቅመን በምናብ ከዘመን ዘመን ሄደን እየመጣን በታሪክ ተቀርፀን ታሪክ ለመቅረፅ ያስችለን ዘንዳ የጀመርናትን ጉዞ እንድናፀናበት በሰባት ገፅ ሰድረን አንድ መልክ ያለዉ ገሚስ ገፅታ (Ep) እንደ አቅማች አበርክተናል ።ዘመን ሚታወሰዉ በጋራ ነዉ እና የሚታወስ ዘመንን ለመፍጠር ሁላችንም በየሙያችን ተሿሹመን መረባረብ አለብን እያልን ድር ቢብር ነዉ እና ተረቱ አብረን ስራችንን በታሪክ እናስቀምጥ እንላለን ። ‘ትናንትን ያወቀ በዛሬ ላይ ቆሞ ነገን ይወጥናል’ ።ነገስታቶች ነን ክብረት ይስጥልን።

አባይ ማዶ የመጀመሪያው በህዝብ ዘንድ እውቅናን ያተረፍንበት ስራችን ነው።

አዋጅ

እንኩ ሰላምታ።
በምንታ ላለ…. በገሚስ ገፅታ።
ምናለ ካላችሁ …. ሰባት ገፅ ያለው ሰባት ሙዚቃ።
። #ባያሌው #Bayalew new Ep
ሁሉም በሙያው ንጉስ ነው። #ነገስታት_ነን

ሰላም ነን ሰላም ይስጣችሁ

ሰላም ብለናል

“ነገስታት” እንባላለን። በሃገራችን የሙዚቃ መንገድ ላይ በወጣትነታችንና ገሀድ በወጣው በሀገር ወዳድ ስሜታችን መነጋገርያ የሆኑና ተወዳጅ ሙዚቃዎችን የምንሰራ በተለይም በመጀመርያው “አባይ ማዶ” በተሰኘው ከ”ቬሮኒካ አዳነ” እንዲሁም ከ”አሉላ አባ ነጋ ” ቲያትር ላይ ትወናው ሀገር ካጨበጨበለት ከ” አማኑኤል የሺወደድ” እና በ”ማለዳ ኮከቦች” የትወና ውድድር ላይ እንዲሁም በተለያዩ ፊልሞች እና የቴሌቭዥን ድራማ ላይ የህዝብ ፍቅር ከተቸረው ከ”ካሳሁን ቦጋለ”ጋር በተጣመርንበት ስራችን ተወዳጅነትን ያገኘን በዩትዮብ ላይም ጥሩ ተመልካቸን በማግኘት የህዝብ ይሁንታን ያገኘን የራፕ ሙዚቃ ስልት አቀንቃኞች ነን። “ነገስታት” በራፐር “አፄ”እና “ቀዳማዊ” በኢትዮጵያውያን አቡሻክር በ2007 የካቲት ወር ላይ በይፋ የተመሰረተ ሲሆን ከስማችን መረዳት እንደሚቻለው የኢትዮጵያ ሙዚቃ ላይ ለመንገስ የተነሳ የተለያየ ጣዕም ያለው ሀገርኛ የራፕ ስልት የምዘፍን ሁለት ራፐሮችን የያዘ የሙዚቃ ቡድን ነው።

ሰላም ይስጣችሁ።

በፈጣሪ ፍቃድ ሆኖ እቅዳችን ቢሳካ ገና ብዙ ያልተነካ አቅም እንዳለን እርግጠኛ ስለሆንን ኢትዮጵያን እና የኢትዮጵያን ሙዚቃ በአፍሪቃ ብሎም በአለም አቀፍ መድረክ ላይ እናስጠራለን ብለን እናስባለን።
ውድ አድናቂዎቻችን እና አድማጭ ተመልካቾቻችን እስካሁን ለሰጣችሁን ክብር እና ፍቅር ከልብ እያመሰገንን “ባንዲራ አዲስ ማፕ ኢንተርቴይመንት” ከተሰኘው የግል ማህበር ጋር በመሆን እንደተለመደው በቀጣይም ሀገርኛ ወጉን እና ትውፊቱን ሳንለቅ አዳዲስ ነገሮችን ይዘን እንደምንመጣ እንገልፅላችኋለን።
ለአብሮነታችሁ ከልብ የመነጨ ምስጋናን ጀባ ብለናችኋል።