አባይ ማዶ

2021 Veronica Adane & Negestat – Abay Mado | አባይ ማዶ

Clip (YouTube)

Deezer

Lyrics

ሸበላው ናማ ወዲህ

አባይ…
አባይ ..አባይ
አባይ … ከወዲያ ማዶ ያለው በሬ
አባይ ማዶ ፊላው ስር
ያለው በሬ ናና ገበሬ
አባይ ማዶ ፊላው ስር
ያለው በሬ ናና ገበሬ

(ግባ በለው)
አባይ ማዶ ፊላው ስር
ያለው በሬ ሲያምር
አባይ ማዶ ፊላው ስር
ያለው በሬ ሲያምር

ተጉዘን ተጉዘን
ከአባይ ማዶ ደርሰን
ሻዩን እንደ አረቄ
በአናት በአናቱ ግተን
ቃምቡሩን እንደውሀ አንስተን ጨልጠን
አምበሬ ጭቃ ገዝተን
ወደቄዬው ዘለቅን

በጨረቃው ጠልሰም በተዋበው አንገቷ
አይኔ ተነድፎ ኖሮ በጫወታ በባቷ
ስታየኝ ኖሯል ለካ ሮጣ ገባች ከቤቷ
እኔም ተከትዬ
ገባሁኝ ሰተት ብዬ

በሰኔ ኩኸኔ
በኩነን አቄነን
በአቄ ሰንደቄ
በሰንደቅ እንድመቅ
ካላቁት ሚልቅ
እነ አይበገር ልብ ውልቅ
ሰፍሮ ከምሮ የወቃ
ምሽት ታዛውን ያነቃ
….አበቃ.

አባይ ማዶ ፊላው ስር
ያለው በሬ ሲያምር
አባይ ማዶ ፊላው ስር
ያለው በሬ ሲያምር

አባይ ማዶ ፊላው ስር ያለው በሬ
ናና ገበሬ

ከማሳው ከወንዙ
ከቀዬው ሲጓዙ
ገራገር ነው ሀገሩ እንኳን ሰው በብዙ
ልክ እንደ ጅረት
በበጋውም በክረምት
አዝመራውም ሞልቶለት
የውጥኑም ሰምሮለት

ባላገሩ ገዳማይ
ማጠፊያ የለው አባይ
በሬውን ከትሞ ካባይ
መናን የሚቀዳው ከላይ

ዘመድ አካል ዘመናይ
ፀባዬ ምግባረ ሰናይ
ሞፈር ቀንበሩን ይዞ ፍቅርን አርሶ ከሰማይ

አርመሰመሰው መሬቱን አርሶ ጨረሰው
በበሬው ጫንቃ ኧረ እኮ ማነው የዳበሰው
አርገበገበው ሰብሉን አፍሶ አጠገበው
ሞፈር ቀንበሩን ኧረ እኮ ማነው የቀበረው

ጓደኛው በሬ
አባቱ ወንዝ ያ ገበሬ
ከትሞላት ለሀገሬ
ዘብ እንዲቆም ለወገኔ

እኔክሽ እኔካ
ቢሰፈርም ቢለካ
ካልነኩት የማይነካ
ገራገር ነበር ለካ

አባይ ማዶ ፊላው ሰር
ያለው በሬ
ናና ገበሬ

ኧረ ጎራው ኧረ ጎራው ኧረ ጎራው

ከወንዙ ብቆም እንስራ አዝዬ
አንድም አንተን ብዬ አንድም ለቄዬ

ኧረ ጎራው ኧረ ጎራው ኧረ ጎራው

የኔ ጢስ አባይ ያኛው ዥረቱ
እንስፍስፍ ቢል እንደ ክረምቱ
ልክ እንደ ሸማው እንደ ጥለቱ
አይጠለፍም ወንዜ በከንቱ

ኧረ ጎራው ኧረ ጎራው ኧረ ጎራው

(የማይደረገውን)

ምነው ለማፈር ተው ቸኮልክሳ
ምነው ለማፈር ተው ቸኮልክሳ
(ይሞክረዋ)
ላይቀር መዋረድ ላይቀር አበሳ
ኧረ ሀገሬ ኧረ ሀገሬ

(ኧረ እምቢኝ እንጃ ኧረ እምቢኝ እንጃ)

ዱብ ዱብ ብሎ እንደበረዶ
ያጊሸን አባይ ዘላለም ወርዶ
አሻግሮ አጥጋቢ ከወዲያ ማዶ
ለኛ ስንዴ ነው ላንዱ ስንደዶ

የገነት ውሀ ይፈሳል አሉ
ከኢትዮጵያ ምድር በቅዱስ ቃሉ
ልጥገብ ልጠጣ ወንዜም የራሴ
አንድም ለጥሜ አንድም ለነብሴ

ፈርኦን የሚሉት ወንዜን ከነካ
ጥቁርነቴን አያውቅም ለካ
እንበለው እና የመጣው ይምጣ
ልክ እንደ ግንዱ ማረፊያውን ይጣ

አባይ ሊደፍር ደርሶ ሊነካ
ከመጣ በሀገር አንገቴን እንካ
ከምላሴ ላይ ፀጉር ይነቀል
አንድም ለአትንኩኝ አንድም ለበቀል

አተተተተተተተ….. በለው
ህህህህህ
አተተተተተተተ
ኤጭ ወዲያ

Soundcloud

Play on Spotify (not available in Ethiopia)