አቡኑ

2022 Negestat feat. Wendi Maru, Samuel Fikadu

Clip (YouTube)

Deezer

Lyrics

በሀገሬ መጣ አሀሀ
በሀገር እምዬ ኤሄሄ
ልሰዋ ለክር ለእምነት ብዬ
በአንድዬ ጌታ በእርሱ ምዬ

አቡን ተሰዋ ለሀገር
አቡን ተሰዋ ለሀገር
አቡን ተሰዋ ለሀገር
አቡን ተሰዋ ለሀገር

አቡን ፀድቆ ባርኮላት አብን ጠርቶ ባራኪ
ልቡን ሰጥቶ ሞቶላት አፈር ገብቶ ማራኪ
ጴጥሮስ አሉት አርበኛው ሰማእት ሆነ ሰባኪ
ፀጋዬ ነው ሰቆቃው ዝክር ገድሉን ተራኪ

ገባ አሉ ያፋሽሽት ገባ አሉ ገዳይ
ግባ በለው ተቀበል ዋ በሀገሬ ጉዳይ
ገባ አሉ ያፋሽሽት ገባ አሉ ገዳይ
ግባ በለው ተቀበል ዋ በሀገሬ ጉዳይ

እኔስ ለሀገሬ ለምዬ ሀገር ለምላት
ጡት ነካሽ አልሆንም እኔ ካጠባኝ ወተት
ልሰዋላት እንጂ እኔም ይፈፀም ትንቢት
አዳፋ ነው ልብሴም እኔም አፈር ነኝ ልሙት

አቡን ተሰዋ ለሀገር
አቡን ተሰዋ ለሀገር
አቡን ተሰዋ ለሀገር
አቡን ተሰዋ ለሀገር

አይፈራም መትረየሱን ሚፈራ ፈጣሪን በቻ
አይሸጣት ችሎ ሀገሩ አይሰፍርም በስልቻ
አቡነ ቄርሎስ አይደለም አቡን ጴጥሮስ ነው ልጇ
የባረካት ነው ምድሪቷን የተሰዋላት ከደጇ

ፊትህ ይሸፈን አትበለው አታርክስ የሰውን ዋጋ
መሞትም ላይቀር ሊለቀስ ነፍስ ሊነጠል ከስጋ
አሉትም እንዳሻክ አርገኝ ደቀመዝሙሬን አትንካ
መቃብሬንም ቆፍረው ጉድጓድ በኔልክ ይለካ

በሀገሬ መጣ አሀሀ
በሀገር እምዬ ኤሄሄ
ልሰዋ ለክር ለእምነት ብዬ
በአንድዬ ጌታ በእርሱ ምዬ

በምህሬ ተድላ ምን ይላሉ ብሸጥ ሀገሬን ላንተ ሰው
ቅኔ የዘረፍኩባትን ቄዬ የተማርኩባት ሰዋሰው
ውግዝ ከመ አርዮስ ህዝብ ለጠላት እንዳይገዛ
አውግዣለሁ በቃሌም እኔ ትረገም ያለበለዚያ

ቅኔ ዘርፌባት ተምሬባት
ሀሁ ብዬባት ቆጥሬባት
እሸት ለቅሜባት በልቼባት
አጋም ቀጋም ብዬም ቦርቄባት

አሀዱ ያልኩባትን ምድር በወፍ ያስተማረቺኝን ዜማ
ዋሽራ የተማርኩባትን አንተ መጥተህ ልትቀማ

መንጋ መርቼባት ባልለያት
አፈር ጭቃ አቡክቼም ለማን ጥያት
አለሁ እኔ ሀገሬ ስኖር ብያት
ሽጬ ክጄ ሀገሬን እንዴት ልያት

አቡን ተሰዋ ለሀገር
አቡን ተሰዋ ለሀገር
አቡን ተሰዋ ለሀገር
አቡን ተሰዋ ለሀገር

Soundcloud

Play on Spotify (not available in Ethiopia)